በዶር. ደብረ ጽዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን አቶ ጌታቸውን ከክልል ፕሬዚዳንትነት አንስቻለሁ አለ

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል

Your browser doesn’t support HTML5

በዶር. ደብረ ጽዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን አቶ ጌታቸውን ከክልል ፕሬዚዳንትነት አንስቻለሁ አለ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ፣ ከዛሬ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ከሥልጣን እንዲወርዱ ወስኛለሁ ሲል በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

አቶ ጌታቸውን ጨምሮ በአወዛጋቢው ጉባኤ ያልተሳተፉ 13 የጊዜያዊ አስተዳደሩ የክልል እና የዞን አመራሮች በህወሓት ተመድበው ከነበሩበት ሥልጣን እንዲወርዱ ወስነናል በማለትም ነው መግለጫው ያስታወቀው።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ በነዶከተር ደብረ ጽዮን ላይ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል፡፡

አስተዳደሩ በመግለጫው፣ ይህ ኃይል በዛሬው ዕለት በይፋ መፈንቅለ መንግሥት አወጇል ሲል ከሷል።