አዲስ አበባ —
ለህወሓት የኢኮኖሚ ምንጭ በመሆን ሲያገለግሉ ነበሩ ያላቸውን 117 የንግድ ድርጅቶች እና መኖሪያ ቤቶች መዝጋቱን የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።
ፖሊስ እርምጃውን የወሰደው በማስረጃ ላይ ተመስርቶ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ጄላን አብዲ ለቪኦኤ ገልጸዋል፡፡
የንግድ ድርጅቶችን የመዝጋት እርምጃው ማንነትን መሰረት ያደረገ እንደሆነ የተለያዩ አካላት ቢገልጹም አቶ ጄላን ይህን ውንጀላ ውድቅ አድርገዋል፡፡
ፖሊስ ዶላርን በጥቁር ገበያ በውድ ዋጋ በመሰብሰብ ለሕወሓት የጦር መሳሪያ ግዢ እንዲውል በማድረግ ላይ ይገኛሉ ያላቸውን በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ለማዋል ከዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል)ጋር እየሰራ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5