በማረቆ ልዩ ወረዳ እና የመስቃን ቤተ ጉራጌ ግጭቶች ሳቢያ የሰላማዊ ሰዎች ግድያ መቀጠሉ ተገለጸ

ኢትዮጵያ

Your browser doesn’t support HTML5

በማረቆ ልዩ ወረዳ እና የመስቃን ቤተ ጉራጌ ግጭቶች ሳቢያ የሰላማዊ ሰዎች ግድያ መቀጠሉ ተገለጸ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን የምስራቅ መስቃን ወረዳ እና በማረቆ ልዩ ወረዳ መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ሳቢያ ካለፈው አርብ እስከ ትላንት በስቲያ እሁድ በነበረው ጊዜ ውስጥ 12 ሰዎች መገደላቸውን ቤተሰቦቻቸው እና ነዋሪዎች አስታወቁ::

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ እንዳሻው ጣሰው በአከባቢዎቹ ላለው የፀጥታ ችግሮችና ሰላማዊ ሰዎች ጥቃት የወረዳዎቹ አመራሮች እጅ እንዳለበት ጠቅሰው የተጠረጠሩም እየታሠሩ መኾናቸውን አረጋግጠዋል:: የሀገር መከላከያ ሰራዊት ወደ አከባቢው መግባቱን የጠቆሙት ነዋሪዎች በበኩላቸው በወንጀሉ የተጠረጠሩ ባለስልጣናትን እና የጦር መሳሪያዎች መያዛቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል::