ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ የትግራይ ተወላጆች ርዳታ እንዳላገኙ ተናገሩ

መቐለ ከተማ

Your browser doesn’t support HTML5

ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ የትግራይ ተወላጆች ርዳታ እንዳላገኙ ተናገሩ

በትግራይ ክልል በተጀመረውና ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ በተሰፋፋው ጦርነት ምክኒያት ወደ ሱዳን ተሰደው የነበሩ የትግራይ ተወላጆች፣ በሱዳን ጦርነት ምክኒያት ወደ አገራቸው ቢመለሱም ርዳታ ማግኘት እንዳልቻሉ ገለጹ።

የክልሉ ማኅበራዊ ጉዳይና መልሶ ማቋቋም ቢሮ በበኩሉ፣ በአቅም እጥረት ምክንያት ተመላሾቹ ርዳታ እያገኙ እንዳልሆኑ ገልጾ፣ “ጉዳዩን ለፌደራሉ መንግሥት አሳውቀናል፣ ከሚመለከታቸው ዓለምአቀፍ ተቋማት ጋራም ተነጋግረንበታል” ብሏል። ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡