የመቀሌ ከተማ ጡረተኞች ዳግመኛ ሰልፍ ወጡ

Your browser doesn’t support HTML5

የመቀሌ ከተማ ጡረተኞች ዳግመኛ ሰልፍ ወጡ

ዛሬ ኀሙስ በመቀሌ ከተማ፣ ሰልፍ የወጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጡረተኞች፣ ለአንድ ዓመት ከመንፈቅ ያህል ጊዜ እንደተስተጓጎለባቸው የገለጹት የጡረታ አበላቸው እንዲከፈላቸው ጠየቁ።

ጡረተኞቹ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ በተመሳሳይ ጉዳይ ሰልፍ ሲወጡ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። የጡረተኞቹ ጥያቄ አግባብነት እንዳለው የገለጸው፣ የፌደራሉ የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጄንሲ ሰሜን ቅርንጫፍ፣ ጉዳዩን ከክልሉ እና ከፌደራል መንግሥት አካላት ጋራ እየተነጋገረበት እንደኾነ አስታውቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።