በሽረ መምህራን ደመወዝ ካልተከፈላቸው ሥራ እንደሚያቆሙ አስጠነቀቁ

Your browser doesn’t support HTML5

በሽረ መምህራን ደመወዝ ካልተከፈላቸው ሥራ እንደሚያቆሙ አስጠነቀቁ

ለሁለት ዓመታት በዘለቀው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት፣ የ17 ወራት ደመወዛቸው እንዳልተከፈላቸው የገለጹ፣ በትግራይ ክልል የሽረ እንዳሥላሴ ከተማ መምህራን፣ ውዝፍ ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው፣ ትላንት እሑድ ባካሔዱት ሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ፡፡

ጥያቄያቸው ካልተመለሰ፣ ሥራ የማቆም ውሳኔ ሊያሳልፉ እንደሚችሉ፣ መምህራኑ አስጠንቅቀዋል፡፡የትግራይ ክልል መምህራን ማኅበር በበኩሉ፣ ሰልፍ የወጡ መምህራን ያሰሙት አቤቱታ፣ “በክልሉ የሚገኙ የ45 ሺሕ መምህራን ጥያቄ እንደኾነ ገልጾ፣ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጣቸው አመልክቷል፡፡ በጉዳዩ ላይ፣ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።