ህወሓት ለነገ የጠራውን የካድሬዎች ስብሰባ እንዲሰረዝ ጊዜያዊ አስተዳደሩ አሳሰበ

Your browser doesn’t support HTML5

ህወሓት ለነገ የጠራውን የካድሬዎች ስብሰባ እንዲሰረዝ ጊዜያዊ አስተዳደሩ አሳሰበ

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)፣ ነገ ቅዳሜ የሚጀመር የካድሬዎች ስብሰባ እንደሚያካሒድ ሲያስታውቅ፤ የክልሉ ጊዜያዊ አስተደዳር በበኩሉ፣ ሒደቱ ሕገ ወጥ እንደኾነ ገልጾ፣ ህወሓት ስብሰባውን እንዲያቆም አሳስቧል፡፡

የታቀደው የህወሓት ካድሬዎች ስብሰባ፣ የትግራይ ሕዝብ ካለበት ችግር ለመውጣት የሚያደርገውን ጥረት የሚያውክ ተግባር እንደኾነ የገለጹት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ “ሊገታ ይገባል” ብለዋል፡፡ የጊዜያዊ መንግሥቱን ሥራ በሚያደናቀፉትም ላይ፣ አስተዳደራቸው አስቸኳይ ርምጃ እንደሚወስድ፣ ፕሬዚዳንቱ አስጠንቅቀዋል፡፡

የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ በመግለጫቸው፣ ፓርቲያችን ከማለት በቀር "ህወሓት" ብለው ሲናገሩ አልተደመጡም፡፡ ስብሰባውን የጠሩት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮችም፣ እነማን እንደሆኑ በስም ለይተው አልጠቀሱም::

ከዚኽ የአቶ ጌታቸው ረዳ መግለጫ በኋላ፣ ለዞኖች አመራሮች ደብዳቤ የላኩት የህወሓት ሊቀ መንበር ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ደግሞ፣ ስብሰባው የተጠራው በፓርቲው ከፍተኛ አመራር ውሳኔ እንደኾነ ጠቅሰው፣ “ጥሪ የተደረገላችኹ ልትሳተፉ ይገባል፤” ሲሉ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩን ማሳሰቢያ ተቃውመዋል፡፡ ደብዳቤው በፓርቲው የፌስ ቡክ ገፅ ላይ የወጣ ነው።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡