በትግራይ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ የወጣቶች ፍልሰት በአሳሳቢ ደረጃ እንደጨመረ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ የወጣቶች ፍልሰት በአሳሳቢ ደረጃ እንደጨመረ ተገለጸ

የትግራይ ክልልን መነሻ ያደረገው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት፣ በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ከቆመ በኋላ፣ የክልሉ ወጣቶች ሕገ ወጥ ፍልሰት በከፍተኛ ቁጥር እንደጨመረ፣ የክልሉ ወጣቶች ቢሮ አስታወቀ፡፡

በወጣቶች ሕገ ወጥ ፍልሰት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ፣ ከትላንት በስቲያ ሰኞ፣ በመቐለ ከተማ ሲካሔድ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው የ113ሺሕ ወጣት ኢትዮጵያውያን ፍልሰት ውስጥ፣ 32ሺሕ የሚደርሱት የክልሉ ወጣቶች እንደኾኑ የዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት (አይኦኤ) ጥናት ማረጋገጡ ተገልጿል።

“ፍልሰቱ የትውልድ ቢባል ይሻላል፤” ሲል ጥናቱን ያጠናከረው የክልሉ የወጣቶች ጉዳይ ቢሮም፣ ፍልሰቱን ለመግታት፥ በተረጋጋ ፖለቲካዊ አመራር ወጣቶችን የሚያሳትፍ ሥርዓት መገንባትና የሥራ ዕድል መፍጠር እንደሚያስፈልግ አሳስቧል፡፡ ቀጣናዊ የስደተኞች ድርጅቱም፣ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና የብዙኀን መገናኛዎች በጋራ እንዲሠሩበት ጥሪ አቅርቧል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።