ዶሮ አርቢ አሜሪካውያን ባለሃብቶች በትግራይ

  • ግርማይ ገብሩ

የተሻሉ የዶሮ ዝርያዎች

ዴቪድ ኤልስ እና ትረንት ኮስቶቮስ የተባሉ አሜሪካውያን ባለሃብቶች ትግራይ፤ መቀሌ ከተማ ውስጥ በሚገኝ የመቀሌ ማዕከል ከህንድ የተገኙ የተሻሉ የዶሮ ዝርያዎችን በዘመናዊ መንገድ በማራባት ላይ ተሠማርተዋል::

ዘንድሮ ግማሽ ሚልዮን የዶሮ ጫጩቶችን ወደ ሞዴል ገበሬዎች ለማዳረስ ተዘጋጅተዋል::

ይህንን ቁጥር በሚቀጥለው ዓመት ወደ አንድ ሚልዮን ከፍ ለማድረግ ማቀዳቸውን ገልፀው “በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት እያንዳንዷ የትግራይ እናቶች ሰላሣ ዶሮዎች እንዲኖሯት እናስችላለን” ብለዋል ዴቪድ ኤልስ::

ትረንት ኮስቶቮስ “እኛ እየሠራን ያለነው በምሳሌነት የሚጠቀስ ማኅበረሰባዊ መዋዕለ-ነዋይን በተግባር ለማሣየት ነው” ይላሉ::

የመቀሌ እርሻ ለረጅም ዓመታት በሞያዊ ክፍተትና በአስተዳደራዊ አቅም ማነስ የሚፈለገውን ውጤት ሳያስመዘግብ መቆየቱን በዚህም መንግሥት በዓመት 15 ሺህ ዶሮዎችን ብቻ ያመርትበት እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል::