በትግራይ ክልል ከአንድ ሺሕ በላይ ሰዎች በረኀብ እንደሞቱ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ ክልል ከአንድ ሺሕ በላይ ሰዎች በረኀብ እንደሞቱ ተገለጸ

በትግራይ ክልል፣ ባለፉት ሦስት ወራት፣ የሰብአዊ ርዳታ ምግብ በመቋረጡ፣ ከአንድ ሺሕ በላይ ሰዎች በረኀብ እንደሞቱ፣ የክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

በተለይ፣ ከአምስት ዓመት በታች የኾኑ ሕፃናት እና የዕድሜ ባለጸጋ አረጋውያን፣ ይበልጥ እየተጎዱ በመኾኑ፣ ከወራት በፊት የተቋረጠው ርዳታ ዳግም እንዲጀመር፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አሳስቧል፡፡

ከዚኹ ጋራ በተያያዘ፣ ተፈናቃዮች እየደረሰባቸው ያለው ሰብአዊ ቀውስ፣ በከፍተኛ ሁኔታ እየተባባሰ እንደኾነም፣ ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።