መቀሌ —
በትግራይ ክልል በመቀሌ ከተማ 05 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተሰብስበው የነበሩ ወጣቶችን ኮሮና ከመከላከል ተብሎ ለመበተን በተደረገው እንቅስቃሴ ግጭት ተከስቶ አንድ ወጣት በፖሊስ ተገደለ ተብሏል።
የዓይን እማኞች ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት የወጣቱ ህይወት ካለፈ በኋላ በተፈጠረው አለመግባባትም በሁለት ወጣቶች ላይ ጉዳት ደርሷል።
በጉዳዩ ላይ ከከተማው ፖሊስ ጽሕፈት ይሁን ሌሎች የሚመለከታቸው መንግሥታዊ መሥርያ ቤቶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5