Your browser doesn’t support HTML5
በመንግሥታዊ መዋቅሩ ላይ ማስተካከያ እያደረገ መኾኑን ያስታወቀው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፣ የዐዲስ ሓላፊዎችን ምደባ ጨምሮ የጊዜያዊ አስተዳደሩን ተግባራት የሚያደናቅፉ አካላትን “በሕግ እጠይቃለኹ ዕንቅፋት ከመፍጠር ይቆጠቡ” ሲል አስጠነቀቀ፡፡
የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ትላንት ረቡዕ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፣ “ሕዝቡን ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ውጤታማ በኾነ መንገድ ለማገልገል ከላይ እስከ ታች የሚያደርገውን ክልላዊ የመዋቅር ማስተካከያ አጠናክሮ ይቀጥላል፤” ብሏል፡፡
ይሕ በእንዲህ እንዳለ በክልሉ የሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አባቶች የጊዚያዊ አስተዳደሩ እና የህወሓት አመራሮች ልዩነት ከሚያባብሱ መግለጫዎች ተቆጥበው ችግራቸውን በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡