በቅዱስ ሲኖዶሱ የተወገዙ የትግራይ ክልል አባቶች ውሳኔውን እንደሚቃወሙና ዳግም እንዲያጤነው ጠየቁ

Your browser doesn’t support HTML5

በቅዱስ ሲኖዶሱ የተወገዙ የትግራይ ክልል አባቶች ውሳኔውን እንደሚቃወሙና ዳግም እንዲያጤነው ጠየቁ

በትግራይ ክልል የሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች እና ሓላፊዎች፣ በአክሱም ከተፈጸመው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እና ሹመት እንዲሁም፣ ‘መንበረ ሰላማ ከፍተኛ ቤተ ክህነት’ በሚል ከሚያደርጉት ክልላዊ እንቅስቃሴ ጋራ በተያያዘ፣ ትላንት፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተላለፈባቸውን ውግዘት፣ “ከንቱ ውግዘት ነው” ሲሉ እንደማይቀበሉት ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ሐምሌ 16 እና 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በአክሱም የተፈጸመውን ሕገ ወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት የሰጡ እና የተቀበሉ፣ እንዲሁም ‘መንበረ ሰላማ’ በሚል በክርስቲያናዊ ትውፊት የማይታወቅ እንቅስቃሴ ያመነጩ እና ያስተባበሩ፥ አራት ሿሚ ሊቃነ ጳጳሳትን፣ ዘጠኝ ተሿሚ መነኰሳትንና ሁለት ሌሎች ግለሰቦችን፥ ከማዕርገ ክህነታቸው በመሻር፣ ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እና አባልነት በመለየት ማውገዙን፣ በትላንትናው መግለጫው አስታውቋል፡፡

ለቅዱስ ሲኖዶሱ የውግዘት መግለጫ መልስ የሰጡት፣ በክልሉ የሚገኙ አባቶች፣ ውግዘቱ፥ የትግራይን ሕዝብ ያለአባት ለማስቀረት የተላለፈ እና በጦርነት ጊዜ የተፈጸመው በደል ቅጥያ ነው፤ ብለዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።