የትግራይ ውክልና በተቋረጠበት ፓርላማ የክልሉ መብቶችና ጥቅሞቿ እንዲጠበቁ ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

የትግራይ ውክልና በተቋረጠበት ፓርላማ የክልሉ መብቶችና ጥቅሞቿ እንዲጠበቁ ተጠየቀ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና በፌዴሬሽን ምክር ቤት ተቋርጦ የቆየው የትግራይ ክልላዊ ውክልና እስኪመለስ በምክር ቤቶቹ በሚወጡ ዐዋጆችና በሚተላለፉ ውሳኔዎች ፖለቲካዊ መብቶቿና ጥቅሞቿ እንዲጠበቁ ለማስቻል ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከፌዴራሉና ከክልል መንግሥታት ጋር እንዲሠራ ባለሙያዎች ጠይቀዋል።

ጦርነቱ ከመቀስቀሱ በፊት በወቅቱ የነበረው የክልሉ መንግሥት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት የነበሩ እንደራሴዎችን “የውክልና ዘመናቸውን ጨርሰዋል” በሚል መልሶ መጥራቱ የሚታወቅ ሲሆን ከዚያ በኋላ ክልሉ በምክር ቤቶቹ ውስጥ ሳይወከል ቆይቷል።

ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ የሕግ ባለሞያዎች በምክር ቤቶቹ ውስጥ የትግራይ ክልል ውክልና አለመኖሩ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ አብራርተዋል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት በሁለቱ ፌዴራል ምክር ቤቶች ውስጥ የትግራይ ተሣትፎ የሌላቸው ልዩ ልዩ ዐዋጆችና ሕጎች እንደወጡ ባለሞያዎቹ አስታውሰው ህጎቹ ትግራይ ውስጥ ስለሚኖራቸው ተፈፃሚነት ወይም ኃይል የራሳቸውን ማብራሪያና ትንታኔ ሰጥተዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን ዘገባ ይከታተሉ።