የሰላም ሚኒስቴር በወቅታዊ ጉዳይ

የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል

በትግራይ ክልል ውስጥ በተካሄደው ጦርነትና ቤንሻንጉል ጉምዝ በመተከል ዞን ውስጥ በተደጋጋሚ በተፈፀሙ ጥቃቶች ለተጎዱ ወገኖች ሰብአዊ ድጋፍ እየደረሰ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር ገልጿል።

የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ሰጭ የሚኒስትሮች ኮሚቴ እየተከታተለው የሚገኘውን የሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ ግንባታ ሥራን አስመልክቶ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ትግራይ ክልል ውስጥ ከ2 ሚሊዮን 500 ሺ በላይ ሰው አፋጣኝ እርዳታ እንደሚፈልግ ተናግረዋል።

ትምህርት በተቋረጠባቸው አካባቢዎችም መልሶ ለማስጀመር መንግሥት እየሠራ መሆኑን ሚኒስትሯ አመልክተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የሰላም ሚኒስቴር በወቅታዊ ጉዳይ