በአበርገለ የጭላ ወረዳ ሰዎች በረኀብ እንደሞቱ የገለጸው አስተዳደሩ ረጂዎችን ተማፀነ

Your browser doesn’t support HTML5

በአበርገለ የጭላ ወረዳ ሰዎች በረኀብ እንደሞቱ የገለጸው አስተዳደሩ ረጂዎችን ተማፀነ

በትግራይ ክልል ማእከላዊ ዞን አበርገለ የጭላ ወረዳ፣ ባለፉት ኹለት ወራት ከመንፈቅ ውስጥ፣ 46 ሰዎች በረኀብ እንደሞቱ፣ የወረዳው አስተዳደር ገለጸ፡፡
ወረዳው፣ ከአሁን በፊት ከፍተኛ ጦርነት እንደተካሔደበት ያወሱት አስተዳዳሪው አቶ ሓጎስ ሃደራ፣ ባለፈው ክረምትም በቂ ዝናም ባለማግኘቱ ረኀቡ እንደተከሠተ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል፡፡
የረኀብ ተጎጂዎችን ለማገዝ በወረዳው የተሰማሩ በጎ ፈቃደኞች መኖራቸውን አስተዳዳሪው ጠቁመው፣ “የማትረፊያ ጊዜው አሁን ነው፤” ሲሉ ረጂ አካላትን ተማፅነዋል፡፡
በክልሉ የሚንቀሳቀሰው “ውድብ ናፅነት ትግራይ” የፖሊቲካ ፓርቲ በበኩሉ፣ ክልሉን ያጋጠመው ረኀብ ትኩረት አልተሰጠውም፤” ሲል ወቅሷል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።