Your browser doesn’t support HTML5
አባላቴ በፖለቲካ እምነታቸው የተነሳ እየታሰሩ፣ እየታገቱ እና እየተንገላቱ ናቸው” ሲል ተቃዋሚው የትግራይ ነጻነት ፓርቲ ውድብ ናፅነት ትግራይ ከሰሰ።
በተለይ ከአወዛጋቢው የህወሐት ጉባኤ በኋላ፣ በክልሉ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የማዕድን እና የመሬት ዝርፊያ የሚቃወሙ አባላታችን ከፍተኛ ችግር እየደረሰባቸው ነው” ሲሉ የፓርቲው ሊቀመንበር ዶክተር ደጀን መዝገበ ተናግረዋል።
ዶክተር ደጀን በሰጡት መግለጫ “አንድ የፓርቲያችን ኣባል ተገድሏል፣ ሌሎች 16 አባላት ደግሞ እስራት፣ እገታ፣ ድበደባ እና እንግልት ደርሶባቸዋል” ሲሉ ወንጅለዋል።
የክልሉ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የሰላም እና ፀጥታ ፅህፈት ቤት ኅላፊ አቶ ተስፋይ አባዲ በበኩላቸው፣ ክሱን ከሐቅ የራቀ ስም የማጥፋት ተግባር በማለት አጣጥለውታል።