በግሪክ ደሴት ጀልባ ሰጥሞ ሦስት ፍልሰተኞች ሲሞቱ አብዛኞቹ አልተገኙም

ፍልሰተኞችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ ጀልባ በግሪክ ሳሞስ ደሴት አቅራቢያ ሰጥሞ የሦስት ፍልሰተኞች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች የደረሱበት እንደማይታወቅ፣ የግሪክ የባህር ጠረፍ ጥበቃ አስታውቋል።

ፍልሰተኞችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ ጀልባ በግሪክ ሳሞስ ደሴት አቅራቢያ ሰጥሞ የሦስት ፍልሰተኞች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች የደረሱበት እንደማይታወቅ፣ የግሪክ የባህር ጠረፍ ጥበቃ አስታውቋል።

ከአጂያን ደሴት በስተሰሜን ምዕራብ ከሚገኘው አጂዮስ ኢሲዶሮስ የተሰኘ ድንጋያማ የባህር ዳርቻ የተነሳው ጀልባ ቢያንስ 30 ሰዎችን አሳፍሮ እንደነበር የባህር ጠረፍ ጥበቃው ጨምሮ ገልጿል።

አንድ የባህር ጥበቃ ባለስልጣን፣ ሞተው የተገኙት ሦስቱም ፍልሰተኞች ሴቶች መሆናቸውን አመልክቷል። አንድ ነፍሰጡር እና ታዳጊ ህፃንን ጨምሮ እስካሁን አምስት ፍልሰተኞች በህይወት መገኘታቸውንና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውንም ሌላ ባለልስጣን ለሮይተርስ ተናግረዋል።

እ.አ.አ ከ2015 ወዲህ ግሪክ ከመካከለኛው ምስራቅ፣ አፍሪካ እና እስያ ተነስተው ወደ አውሮፓ ህብረት ለሚጓዙ ፍልሰተኞች ተመራጭ መተላለፊያ ሆናለች፡፡ ከ2015 እስከ 2016 በነበረው ጊዜ ብቻ ወደ አንድ ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በደሴቶቿ ላይ አርፈዋል። አብዛኞቹ ፍልሰተኞች አየር የሚሞሉ እና የሚተነፍሱ ጀልባዎችን እንደሚጠቀሙም ተመልክቷል።