የኤርትራ ወታደሮች አድዋ ላይ ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውን አምነስቲ ገለፀ

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሰኞ ሚያዚያ 4 /2013 ዓ.ም የኤርትራ ወታደሮች በዐድዋ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከፍተው ሦስት ሰዎች መግደላቸውን እና 19 ማቁሰላቸውን የዐይን እማኞቹ ጠቅሶ ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ። በሌላ በኩል ድርጊቱ መፈፀሙን አንድ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባለሥልጣን ለሮይተርስ የዜና ወኪል አረጋግጠዋል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የዐይን እማኞቹ የነገሩትን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የኤርትራ ወታደሮች የዐድዋ ከተማን ሲያቋርጡ ዋና መንገድ ላይ በሚገኝየአውቶብስ መናህሪያ አካባቢ በሚገኙ ሰዎች ላይ ተኩስ ከፍተዋል ብለዋል።

“በኤርትራ ወታደሮች በደረሰው ሌላ ጥቃት ምክኒያት ሦስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል 19 ደግሞ ቆስለው በሆስፒታል ይገኛሉ” ያሉት የድርጅቱየምስራቅ አፍሪካ እና የአፍሪካ ቀንድ ምክትል ዴሬክተር ሳራ ጃክሰን “በሰላማዊ ሰዎች ላይ ሆን ተብለው የሚፈፀሙ ጥቃቶች በዓለም አቀፍየሰብዓዊ መብቶች ሕግ የተከለከሉ በመሆናቸው በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል” ብለዋል።

በሌላ በኩል ሮይተርስ የዜና ወኪል የአካባቢውን ባለሥልጣን ጠቅሶ የተገደሉት ሰዎች ዘጠኝ መሆናቸውን ዘግቧል። አስተያየታቸውን ለሮይተርስየሰጡት የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደርና የአካባቢው ባለሥልጣን ብርሃነ ገብረጻዲቅ፤ በዐድዋ ከተማ የተፈፀመውን ጥቃት ለመከላከልየኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጣልቃ ገብቷል ብለዋል።

የኤርትራ ወታደሮች ሰላማዊ ዜጎችን መግደላቸውን ገልፀው፤ የኢትዮጵያ ወታደሮች ጣልቃ ባይገቡ ኖሮ ተጨማሪ ሰላማዊ ሰዎች ይገደሉ ነበር ሲሉ ለሮይተርስ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል፤ በጹሑፍ በሰጡት ምላሽ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል ውስጥ የኤርትራ ወታደሮችመኖር አለመኖራቸውን በተመለከተ በቀጥታ ምላሽ ባይሰጡም በአጠቃላይ የኤርትራ ወታደሮች ሰላማዊ ሰዎችን በፍፁም አይገድሉም ብለዋል።

አምነስቲ በበኩሉ ስድስት የዐይን እማኞቹን ጠቅሶ ባወጣው ሪፖርት ፤ በጥቃቱ ከቆሰሉት የተወሰኑ ሰዎች አድዋ ከተማ ውስጥ ዶን ቦስኮ ወደተባለሆስፒታል ተወስደው እንደነበርና 19ኙ ደግሞ ለተጨማሪ ሕክምና ወደ አክሱም ሆስፒታል መላካቸውን በመግለጫው ላይ አስፍሯል።

በሌላ በኩል እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ከ2020 ከታኅሣሥ አጋማሽ ጀምሮ ትግራይ ውስጥ የሕክምና እርዳታ እየሰጠ እንደሚገኝያስታወሰው ዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ማኅበር (MSF) የምስራቅ አፍሪካ ክፍል በትዊተር ገፅ ላይ እንዳሰፈረው ፤ ሰኞ ረፋድ ላይ 18 ሰዎችጉዳት ደርሶባቸው ኪዳነምህረት ወደ1 ተባለ ሆስፒታል እንደመጡና የ11ዱ ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ወደ አክሱም ሆስፒታል እደተላኩ አስፍሯል።የቆሰሉት ሰዎች ደግሞ በዐድዋ የአውቶብስ መናህሪያ አካባቢ ወታደሮች በከፈቱባቸው ተኩስ መቁሰላቸውን እንደነገሯቸው ገልፀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የኤርትራ ወታደሮች አድዋ ላይ ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውን አምነስቲ ገለፀ