ሲቪሎች በሶሪያ ምሥራቃዊ ጎታ አካባቢ እየሸሹ ነው

  • ቪኦኤ ዜና
በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሲቪሎች ዛሬ በሶርያው ምሥራቃዊ ጎታ ወደ ምትገኘው ከተማ እየሸሹ ናቸው።

በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሲቪሎች ዛሬ በሶርያው ምሥራቃዊ ጎታ ወደ ምትገኘው ከተማ እየሸሹ ናቸው። ብሪታንያ ሆኖ የሶርያን ጉዳይ የሚከታተለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን እንደሚለው የሶርያ ወታደራዊ ኃይል በአካባቢው ወደ መጨረሻው በአማፅያን ቁጥጥር ሥር ወዳለው ቦታ እየገፋ ነው።

የሰብዓዊው መብት ቡድን ሥራ አስኪያጅ ራሚ አብደልራሕማን የመንግሥት ኃይሎች ደማስቆ አጠግብ ያለውን አካባቢ ለማስመልስ ባለፈው ወር የማጥቃት ዘመቻ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ይህን ያክል ብዛት ያላቸው ሰዎች ሲውጡ ለመጀመርያ ጊዜ ነው ብለዋል።

ሌሊቱን የሶርያ ወታደራዊ ኃይሎች ገፍተው ወደ አካባቢው እንደገቡ ለሲቪሎቹ መውጫ መሥመር ከከፈቱ በኋላ ሲቪሎቹ በሶርያ መንግሥት ቁጥጥር ሥር ወዳለው ቦታ በእግር፣ በመኪኖችና በሞተር ብስክሌቶች እንደጎረፉ ተገልጿል።