ሞዛምቢክ ውስጥ የጽንፈኛ እስላማዊ ጥቃቱ አገርሽቷል፣ በሺዎች የተቆጠሩ እየተሰደዱ ነው

ካቦ ደልጋዶ ክፍለ ግዛት የተፈናቀሉ ቤተሰቦች ከታጠቁ አማፂያንን እየሸሹ እአአ ሰኔ 14/2022

ካቦ ደልጋዶ ክፍለ ግዛት የተፈናቀሉ ቤተሰቦች ከታጠቁ አማፂያንን እየሸሹ እአአ ሰኔ 14/2022

ሰሜን ሞዛምቢክ ውስጥ ሰሞኑን ከተከሰተው የጽንፈኛ እስላማዊ ጥቃት በተያያዘ ቢያንስ ሰባት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ። ከአስር ሺህ የሚበልጡ ሰዎች ቀያቸውን ጥለው መሰደዳቸውን የተመድ አስታውቋል። ጥቃቱ የደረሰው እአአ በ2017 ደም ያፋሰሰ ዐመጽ በተቀሰቀሰበት በነዳጅ በከበረው ካቦ ደልጋዶ ክፍለ ግዛት መሆኑ ተገልጿል። አመጹን ተከትሎ ባለፈው ዓመት የደቡባዊ አፍሪካ ክልላዊ ወታደራዊ ኃይል ተሰማርቶ በመጠኑ ሰላማዊ ድባብ ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል።

ሰሞኑን ባገረሸው ጥቃት ናቱፒል በተባለ መንደር አራት ሰዎች አንገታቸው ተቀልቶ መገደላቸውንና ጥቃቱ ያስሸበራቸው ነዋሪዎች መንደሩን ለቀው መሰደዳቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቦ አንድ ነዋሪ "ከቀያቸው የሸሹ ሌሎች ነዋሪዎች ያነሱትን ፎቶ ግራፍ ስላየሁ ድርጊቱ መፈጸሙን አረጋግጫለሁ" እንዳሉ አመልክቷል።

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ተጠርጣሪ ጽንፈኛ ታጣቂዎች የአውስትራሊያዊ ንብረት የሆነ ማዕድን ማውጫ ሁለት ሰራተኞችን መግደላቸው ተዘግቧል።