በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር ቶማስ ግሪን ፊልድ በኢትዮጵያ ያላው የሰብዓዊ ሁኔታ እጅግአሳሳቢ መሆኑን መሆኑን ገለፁ። አምባሳደር ግሪንፊልድ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳዮች ሴኔት ኮሚቴ የእጩዎች መስማት ሂደት ላይ የኢትዮጵያን ጉዳይ በተመለከተ ተጠይቀው፤ “በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እጅግአሳስቦኛል። ከሦስት ዓመት በፊት ይቺን አገርና አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትሯን እያከበርን ነበር። ወደ ፊትየመራመድ ዕድል ስለገጠማቸው ለሕዝባቸው ብልፅግና የሚያመጡበት ጊዜ ነው ብለን ደስ ብሎን ነበር።አሁን ከራሳቸው ሕዝብ ጋር ጦርነት ላይ ናቸው። የተባበሩት መንግስታት ሁኔታውን ቀረብ ብሎ ዓይቶ እንዴትምላሽ መስጠት እንዳለበት ማየቱ አስፈላጊ ነው።” ብለዋል።
አያይዘውም፤ “በተለይ የሰብዓዊ ሁኔታው እጅግ አሳሳቢ ነው። ስለዚህ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶችናሠራተኞች በትግራይ ክልል ውስጥ ያለውን ሁኔታ እንዲያዩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለብን። በተጨማሪም ምን እየተካሄደ እንዳለ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በጣም ግልፅና ቀጥተኛ የሆነ ውይይት ማካሄድ፣ እያደረጉ ያሉት ነገር ነገር እንዲቆም መወትወትና ግጭቱ እንዲጠናቀቅ ማድረግ አለብን ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም በቀጠናው ላይ ሰፊ የሆነ ተፅእኖ እያሳደረ ነው።” ብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5