“የምርጫውን ውጤት ለመቀበል ቃል አልገባም” - ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ

  • ሰሎሞን ክፍሌ

ፎቶ ፋይል

በመጪው ወር በሚካሄደው ምርጫ ከተሸነፍኩ የምርጫው ውጤት ተጭበርብሯል ማለት ነው ማለታቸው ተነቅፏል።

የሪፑብሊካን ፓርቲው እጩ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት ማታ ከዲሞክራቷ ሂለሪ ክሊንተን ጋር ባደረጉት ሦስተኛውና የመጨረሻው ክርክር ላይ፥ የምርጫውን ውጤት ለመቀበል ቃል አልገባም ብለዋል።

ሂለሪ ክሊንተንና ዶናልድ ትራምፕ በፕሬዘዳንታዊ ምርጫው ክርክር ወቅት

ሁለቱ የዋይት ሃውስ ቤተ መንግሥት ተስፈኞች ላስቬጋስ ኔቫዳ ባደረጉት በትላንቱ ክርክራቸው ወቅት በተጨማሪ፥ ሩሲያን፥ ፍልሰተኞችንና ለዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በሚሰየሙት ዳኛ አመራረጥ ላይ ተጋጭተዋል።

ባልደረባችን ጄም ማሎኒ ከዋሺንግተን የአንድ ሰዓት ተኩሉን ውይይት ጨምቆ አዘጋጅቶታል።

የደጋፊዎች አስተያየቶችም ታክሎበታ፤ ሰሎሞን ክፍሌ ያቀርበዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

“የምርጫውን ውጤት ለመቀበል ቃል አልገባም” - ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ