በትግራይ የሚካሄደው ጦርነት እየሰፋ ሄዷል

ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ

በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት እየሰፋና እየተባባሰ መምጣቱ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የሰላም ተቋም የአፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት አሊ ቨርጂ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የሰላም ተቋም የአፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት አሊ ቨርጂ ከአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ቺነዱ ኦፎር ጋር ባደረጉት ቆይታ በሰሜን ኢትዮጵያ በአንድ አቅጣጫ ይደረግ የነበረው ጦርነት አሁን በሁለት ቦታ መከፈሉን ገልፀዋል።

አንደኛው የጦርነቱ ቦታ ከአማራ ክልል ጋር በሚዋሰነውና ወደ ሱዳን በሚወስደው ምዕራብ እና ደቡብ ትግራይ ላይ ሲሆን ሁለተኛውና አዲስ የተጀመረው ደግሞ ትግራይና አፋር ክልሎች መሀል ወደ ጅቡቲ በሚወስደው አቅጣጫ መሆኑን አማካሪው አብራርተዋል።

ዘጋቢያችን ቺነዱ ኦፎር ከቨርጂ ጋር ያደረገውን ቆይታ ስመኝሽ የቆየ ታቀርበዋለች።

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ የሚካሄደው ጦርነት እየሰፋ ሄዷል