ገና በአፍላ ዕድሜው ያደረበትን የሙዚቃ ፍቅር ይዞ አደባባይ የወጣው አንጋፋው ድምጻዊ ማህሙድ አህመድ ትውልድ ተሻግረው ዛሬም ድረስ እንደ አዲስ የሚሰሙ ሙዚቃዎችን እየተጫወተ እዚኽ ደርሷል። የኢትዮጵያን የሙዚቃ ባህል በዓለም አቀፍ የሙዚቃ መድረኮች ማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን፤ ሙዚቃውን የሚጫወቱ ቁጥራቸው የበዙ አውሮፓውያን እና አሜሪካውያን ሙዚቀኞችም አፍርቷል።
Your browser doesn’t support HTML5
ዩናይትድ ስቴትስን እና ካናዳን ጨምሮ በአንዳንድ ሀገሮች ዛሬ የሚከበረውን የምስጋና ቀን ክብረ በዓል ምክኒያት በማድረግ፣ በዋሽንግተን እና አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን “ለዕድሜ ዘመን አገልግሎትህ፣ በድንቅ ሙዚቃ ሥራዎችህ ለሰጠኽን ደስታ እና ብሎም የባሕል አምባሳደር ሆነህ አገር ላስተዋወቅክበት ውለታህ እናመሰግናለን” ሊሉት ተሰናድተዋል። ማህሙድ እስካኹን ከኖረበት ዕድሜ፣ አብላጫው ያገለገለበትን መድረክ የሚሰናበትበት ይህን ልዩ ዝግጅት ‘አክብረን እንከበር’ የሚል ሥያሜ ሰጥተውታል።
አቶ ፍስሃ ወልዴ የሥነ ሥርዐት አስተባባሪ ናቸው። ለዝግጅቱ መነሻ የሆናቸውን አጋጣሚ ጨምረው በመድረኩ የታሰበውን በመጠኑ ያጋሩናል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።