ኢትዮጵያ ውስጥ በ1960ዎቹ መጨረሻ ላይ በተካሄደው ቀይ ሽብር ውስጥ እጃቸው አለ የተባሉ ኢትዮጵያዊ ሆላንድ ውስጥ ተይዘው አንድ የሄግ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ኢትዮጵያ ውስጥ በ1960ዎቹ መጨረሻ ላይ በተካሄደው ቀይ ሽብር ውስጥ እጃቸው አለ የተባሉ ኢትዮጵያዊ ሆላንድ ውስጥ ተይዘው አንድ የሄግ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ሮይተርስና የፈረንሣይ የዜና ወኪል - ኤኤፍፒ ባሠራጯቸው ዘገባዎች መሠረት እሸቱ ዓለሙ የሚባሉት የ63 ዓመት ዕድሜ ተጠርጣሪ በወቅቱ የሃገሪቱ መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ተሹመው ጎጃም ክፍለ ሃገር ውስጥ በነበሩ ጊዜ በ197ዐ ዓ.ም. ሰባ አምስት ወጣት እሥረኞች እንዲገደሉ ትዕዛዝ ሰጥተዋል የሚል ክሥ ተመሥርቶባቸዋል።
Your browser doesn’t support HTML5
ሆላንድ ውስጥ ጥገኝነት ጠይቀው ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት እዚያው እየኖሩ ያሉት እሸቱ ዓለሙ በተጨማሪም ከሁለት መቶ በሚበልጡ ሰዎች ላይ ጅምላ እሥራትና ማሳደድ በማካሄድ፣ እንዲሁም ኢሰብዓዊ አያያዝ በመፈፀም ተከስሰዋል።
አቶ እሸቱ የእምነት ክሕደት ቃላቸውን በችሎት ፊት በሰጡበት ወቅት የተከሰሱባቸውን አድራጎቶች እንዳልፈፀሙ ተናግረዋል።
አቶ እሸቱ በቀይ ሽብር ወቅት ፈፅመዋቸዋል ለተባሉ ጥፋቶች ጉዳዩን በሌሉበት ያየው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ አስተላልፎባቸው እንደነበረ የዜና አውታሮቹ ዘገባዎች ጠቁመዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5