አቃቤ ሕግ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎና በሃያ ሦስት እሥረኞች ግድያ፣ በሰላሳ ስምንት ታራሚዎች ላይ የሽብር ክስ መሥርቷል

  • መለስካቸው አምሃ

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

ተጠርጣሪዎቹ "በምርመራ ወቅት ከባድ የማሰቃየት ድርጊት ተፋጽሞብናል" ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አቤት ብለዋል፤ ፍርድ ቤቱም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሌላ በኩል ደግሞ የቀድሞውን የአንድነትና የሠማያዊ ፓርቲ አመራር አባላትን ጨምሮ ሦስት መልስ ሰጪዎችን በነፃ ሲያሰናብት ሁለቱን ደግሞ የተከሰሱበትን፣ አንቀፅ ለውጦ እንዲከላከሉ ወስኗል።

ነሐሴ 28/2008 ዓ.ም. በፌዴራል ማረሚያ ቤት ቅሊንጦ እስር ቤትን በማቃጠልና ሃያ ሶስት እስረኞችን ሕይወት በማጥፋት እንዲሁም በሚሊዮኖች ብር የሚገመት ንብረት በማውደም ፌዴራል አጠቃላይ አቃቢ ሕግ በሰላሳ ስምንት አስረኞች ክስ ምስርቷል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

አቃቤ ሕግ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎና በሃያ ሦስት እሥረኞች ግድያ፣ በሰላሳ ስምንት ታራሚዎች ላይ የሽብር ክስ መሥርቷል