“አንድ ሰው በፖሊስም ሆነ በሌላ የሕግ አስፈጻሚ አካል ለሚቀርብለት ጥያቄ፤ ካልፈቀደ በስተቀር መልስ ያለመስጠት መብት አለው።” አቶ ደረጀ ሰምሴ ቡልቶ፤ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሞያ።
Your browser doesn’t support HTML5
አንድ ዜጋ በፖሊስ ወይም በሌላ የሕግ አስፈጻሚ አካል ለሚቀርብለት ጥያቄ መልስ ለመስጠት ወይም ላመስጠት የሚወሰድ የግል ምርጫና ውሳኔ በሕግ ዓይን እንዴት ይታይ ይሆን?
ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት በሁለቱ ወንድማማቾች Dzhokhar እና Tamerla Tsarnaev በቦስተን ማራቶን የደረሰውን የቦምብ ፍንዳታ ተከትሎ “ለመርማሪዎች ዋሽቷል፤” በሚል የተወነጀለውና የፍርድ ሂደቱ ለሳምንታት ሲታይ የቆየው ሮቤል ፊሊጶስ ከትላንት በስቲያ ከቀረቡበት ክሶች በሁለቱ ጥፋተኛ ሆኖ ተበይኖበታል።
ሮቤል ጥፋተኛ የሆነበትን “ለመርማሪዎች የሃሰት መረጃ የመስጠት ወንጀል፤” ጉዳይ መነሻ በማድረግ፤ ለመሆኑ ዜጎች ለሕግ አስፈጻሚዎችና መርማሪዎች መረጃ የሚጠየቁበትን ሁኔታዎችና መንገዶች አስመልክቶ የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ ምን ይላል?
የዜጎች መብት፤ የሕጉ ጥበቃና አስገዳጅነት፤ ቀጣዩ ቃለ ምልልስ የሚያተኩርባቸው ጭብጦች ናቸው።
ትኩረት ላደረግንበት ለዚህ ጭብጥ መነሻ በሆነን የሮቤል ፊልጶስ ጉዳይ ተከላካይ ጠበቃው የነበሩትን አቶ ደረጀ ሰምሴ ቡልቶን አወያይተናል። ሙሉውን ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ፤