የዩንቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች ዕጣ ፈንታ

Your browser doesn’t support HTML5

የዩንቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች ዕጣ ፈንታ

በ2016 ዓ.ም የ12 ክፍል መልቀቂያ ፈተናየዩንቨርስቲ መግቢያ ውጤት ላላመጡ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ተማሪዎች መንግስት ከወዲሁ መፍትሄ ካላመጣ ከፍተኛ ማህበራዊ ቀውስ ሊፈጠር እንደሚች ተገለፀ:: የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ተማሪና ወላጆች መንግስት የዩንቨርስቲ መግቢያ ውጤት ላላመጡ ተማሪዎችን ልዩ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ብለዋል::

በሌላ በኩል የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ካለፉት ዓመታት ተሞክሮዎቹ በመማር ለተማሪዎቹ የተሻለ የስልተና አማራጮች እና የስራ ዕድል ዝግጅት አድርጎ ለመቀበል መሰናዳቱን ለአሜሪካ ድምጽ አስታውቋል፡፡ በአስቴር ምስጋናውና በኤደን ገረመው የተዘጋጀው ዘገባ ይኸንን ይቃኛል፡፡