በኢትዮጵያ መደበኛ ባልሆነው የውጭ ምንዛሬ ገበያ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በፍጥነት የዶላር ምንዛሬ መቀነሱን፤ የገበያው ተዋናዮችና የምጣኔ ሀብት ተንታኞች በመግለጽ ላይ ናቸው።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያ መደበኛ ባልሆነው የውጭ ምንዛሬ ገበያ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በፍጥነት የዶላር ምንዛሬ መቀነሱን፤ የገበያው ተዋናዮችና የምጣኔ ሀብት ተንታኞች በመግለጽ ላይ ናቸው።
በባንክ 27 ብር ከ30 ሳንቲም የሚመነዘረው የአሜሪካ ዶላር ከከረመበት የአስር ብር የገበያ ጭማሬ ወደ ግማሽ በሚሆን ሲቀንስ ተስተውሏል።
ለመሆኑ ለዚህ ፈጣን የምንዛሬ ውድቀት ምክንያቶች ምንድን ናቸው። ሔኖክ ሰማእግዜር ያነጋገረው የምጣኔ ሀብት ተንታኝ ጌታቸው ተክለማርያም፤ በመደበኛ ገበያው ምንም አይነት የፖሊሲ ለውጥ ሳይታይ መደበና ያልሆነው ጥቁር ገበያ ውስጥ የታየው ለውጥ ከገበያ መላምቶች ጋር የተያያዘ ነው ይላል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5