Your browser doesn’t support HTML5
Your browser doesn’t support HTML5
“በዝምታ ከተዋጡት ቤቶች ይልቅ በግሩም ሙዚቃ በደመቁት ቤቶች የፍቅር ቅመሙ ይጨምራል።”ሲል ይንደረደራል::
አስገራሚው የሙዚቃ ምስጢር እና ፋይዳ! የሙዚቃ ዓለም ወግ ነው የሙዚቃን ፍቅር እና ቁጥራቸው የበዙ ትሩፋቶቹን መልከት የምናደርግበት!
ግሩም የሙዚቃ ሥልቶች ሆን ተብሎ በሚደመጥባቸው ቤቶች (የዝምታ ድባብ ካረበባቸው ይልቅ) ፍቅር ይደምቅባቸዋል።
ሙዚቃ መሰማቱ ብቻ ሳይሆን ታዲያ “ሆን ተብሎ” መሆኑ ላይ ነው ሚስጥሩ .. እንደ ጥናቶቹ ምልከታ።
“ሙዚቃ የሌለበት ህይወት ስህተት ይሆናል።” ፍሬዴሪክ ኒቸ
"የሙዚቃን ፍቅር አጣፋጭነት መቼስ ማን ያጣዋል?" ይባል ይሆናል። “ዝምታ የሰፈነበትን የሁለት ፍቅረኞች የመጀመሪያ የእራት ምሽት ግን ምን ይሉታል?” ሲል ይጠይቃል አንድ ታዛቢ።
ሙዚቃ ስሜታችንን ለማሳመር .. ቀልባችንን ለማስከን .. አለያም ከዕለታት በአንዱ በቁጣ ስሜት ስንጎብኝ .. ያን ድንገት እንደ ደራሽ ውሃ ሳይጠብቁት የመጣ ቁጣ ለማርገብ አንዳች ልዩ አቅም የታደለ መሆኑን ልብ ብለብ እንደሁ .. ወይ እብደ መሸሸጊያ የማድርግ ልማድ አንዱ መንገዳችን ወደ መሆን ተቃርቦ ከሆነ? .. በቤት ውስጥ የምናሳልፋቸው ሙዚቃ አልባ ምሽቶችና የእረፍት ጊዜያት መብዛታቸው ግን በእርግጥ ጥያቄ ማጫሩ አልቀረም::
ለሁሉም እስኪ ሆን ብለን ጥቂት የሙዚቃ ቅመም ከህይወታችን .. ከምሽትና ከእረፍት ቀኖቻችን እንደ ጣዕም ማጣፈጫ ነስነስ እናድርግ እና የሚሆነውን እንይ።