የቴክሳስ ባለሥልጣናት “ድንበር ጥሰው የሚገቡ” የሚሏቸውን ፍልሰተኞች እየያዙ ለመመለስ እንዲያስችላቸው ያወጡትን ሕግ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለጊዜውም ቢሆን አግዶታል።
ይሁን እንጂ በሥር ፍርድ ቤቶች በይግባኝ እየታየ ያለው ጉዳይ እስኪጠናቀቅ የቴክሳስ ግዛት መንግሥት እርምጃውን እየወሰደ መቆየት እንዲችል “ጊዜያዊ ፈቃድ” የሰጠም ይመስላል።
Your browser doesn’t support HTML5
ሕጉ የሃገሪቱን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይሁንታ ካገኘ ፖሊስና ሌሎችም ሕግ አስከባሪዎች ሰዉን እንዳሻቸው እያስቆሙ እንዲጠይቁ ሥልጣን ይሰጣቸዋል። በዚህ ደግሞ የመኖርያ ፍቃድና ዜግነት ያላቸው ሰዎችም ሳይቀሩ፤ በተለይ ደግሞ “በዘራቸው የተለዩቱ ሁሉ ሊጉላሉ ይችላሉ” በሚል ሥጋትና ተቃውሞ እየተሰማ ነው።
የቴክሳስ ህዩስተን ነዋሪውና የከተማዪቱ የቀድሞ ሸሪፍ (የፀጥታ ሹም)፣ አሁን የቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ ፖሊስ መምሪያ ባልደረባ አቶ ኃይሌ ተፈራና ዋሽንግተን ዲ.ሲ. ውስጥ ደግሞ ጠበቃው አቶ ዳንኤል ውብሸት የሃገሪቱን የሚግሬሽን ጉዳዮች በውል ያውቃሉ፤ ስለዚህ ስለሰሞኑም ጉዳይ አነጋግረናቸዋል።
ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ።