በቴፒ በተቀሰቀሰ ግጭት 10 ሰዎች ተገደሉ

ቴፒ

ቴፒ

በቴፒ ከተማ በዛሬው ዕለት ዳግም በተቀሰቀሰ ግጭት 10 ሰዎች መገደላቸውን የከተማው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በሌላ በኩል አምስት ሰዎች መገደላቸውንና ቁጥራቸው ያልታወቁ በርካታ ሲቪሎች መቁሰላቸውን የከተማው ፍትህና ፀጥታ አስተዳደር አመልክቷል፡፡

በቴፒ ከተማ በዛሬው ዕለት ዳግም በተቀሰቀሰ ግጭት 10 ሰዎች መገደላቸውን የከተማው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በሌላ በኩል አምስት ሰዎች መገደላቸውንና ቁጥራቸው ያልታወቁ በርካታ ሲቪሎች መቁሰላቸውን የከተማው ፍትህና ፀጥታ አስተዳደር አመልክቷል፡፡

የግጭቱ መንስዔ ከሥልጣንና ራስን በራስ ከማስተዳደር ጋር የተያያዘ የማንነት ጥያቄ ነው ተብሏል፡፡ ከዚህ በፊት የፀጥታ ችግር በፈጠሩ ግለሰቦች ላይ ዕርምጃ ያለመውሰድ እና የህግ የበላይነትን ያለማስከበር ግጭቱ ዳግም እንዲቀሰቀስ አድርጓል ነው የተባለው፡፡ በከተማው አሁንም ውጥረት እንዳለና ቱኩስ እንደሚሰማ የከተማው ነዋሪዎች ይናግራሉ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በቴፒ በተቀሰቀሰ ግጭት 10 ሰዎች ተገደሉ