በጦርነት የተጎዱ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች እንደሚጠገኑ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ አስታወቀ

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዲሬክተር ኢንጂነር ባልቻ ሬባ

Your browser doesn’t support HTML5

በጦርነት የተጎዱ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች እንደሚጠገኑ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ አስታወቀ

በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን ለመጠገን ማቀዱን የኢትዮጵያ ኮምዩኒኬሽንስ ባለሥልጣን አስታወቀ። የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዲሬክተር ባልቻ ሬባ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለመጠይቅ፣ ተቋማቸው በጦርነት የተጎዱ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባትና ሌሎችም ተያያዝ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን፣ የ80 ሚሊዮን ዶላር በጀት መያዙን አመልክተዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ አንድ የንግድና ኢንቨስትመንት ባለሞያ ደግሞ፣ በቴሌኮም መሰረተልማቶች ላይ እየደረሰ ያለው ውድመት፣ በልዩ ልዩ ዘርፎች የአገልግሎት መጓደልን እያስከተለ መሆኑን ገልጸዋል። የመልሶ ግንባታ ሥራውም ከውጭ ምንዛሪ ጋራ የተያያዘ በመኾኑ ቀላል እንደማይኾን አብራርተዋል።