ቴል አቪቭ እና አካባቢው ያለው ሁኔታ

ዶ/ር ጸጋ ፈንታሁን መላኩ የእስራኤል ኪነሴት (ፓርላማ) አባል (ሊኩድ ፓርቲ)

Your browser doesn’t support HTML5

ቴል አቪቭ እና አካባቢው ያለው ሁኔታ

የመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረት ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ ኢራን በዛሬው ዕለት ቁጥሩ ወደ 180 የሚጠጋ ሚሳኤል ወደ እስራኤል ተኩሳለች፡፡ ይሁንና በሚሳኤሎቹ ጥቃት እስካሁን የደረሰ ጉዳት አልተዘገበም፡፡ በሌላ በኩል በቴል አቪቭ በተኩስ እና በስለት በተፈፀመ ጥቃት ቢያንስ ስድስት ሰዎች ሲገደሉ ዘጠኝ ደግሞ ቆስለዋል።"ሽብርተኞች" ብሎ በገለጻቸው ሁለት ግለሰቦች ጥቃቱ እንደተፈፀመ የእስራኤል ፖሊስ አስታውቋል።

እንዲህ ባለው የሚሳኤል ጥቃት ወቅት እንደሚያደርጉት ሁሉ በዛሬውም የኢራን ጥቃት ዜጎች መሸሸጊያዎች ውስጥ ገብተው ቆይተዋል፡፡ ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት የቴል አቪቭ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመጠየቅ የአሜሪካ ድምጽ በስልክ ደውሎ ያነጋገራቸው የእስራኤል ፓርላማ (ኬኔሴት) አባሏ ዶ/ር ጸጋ ፈንታው መላኩን አነጋግሯል፡፡