Your browser doesn’t support HTML5
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎና ሰሜን ሸዋ ዞኖች የሚገኙ መምህራን የጸጥታ ችግር ወደአለባቸውና ወደተመደቡባቸው የገጠር ት/ቤቶች ሄደው ሥራ እንዲጀምሩ በአካባቢው ባለሥልጣናት አስገዳጅ መመሪያ እንደወጣባቸው ገለጹ፡፡
መምህራኑ የተመደቡባቸው ቀበሌዎች በፌደራል መንግሥቱ እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከፍተኛ ግጭት የሚካሄድባቸው በመኾናቸው ለደህንነታቸው እንደሚሰጉ ተናግረዋል፡፡ እንዳይቀሩ ደግሞ ወደምድብ ቦታቸው ካልሄዱ ደሞዝ እንደማይከፈላቸው እንደተነገራቸው ገልጸዋል፡፡ መምህራኑ በዚህ መሃል ችግር ላይ መውደቃቸውን አመልክተው የጸጥታው ሁኔታ እስኪስተካከል መንግሥት ችግራቸውን እንዲረዳላቸው ጠይቀዋል፡፡
የአማራ ክልል መምህራን ማኅበር በመምህራኑ ስለተነሳው ቅሬታና ስጋት መረጃ እንዳለው ጠቅሶ በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ አካላት የመማር ማስተማሩ ሂደት ከጸጥታ ችግር የጸዳ እንዲሆን በማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲያበረክቱ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡