አዲስ አበባ —
ጣይቱ ሆቴል - ቃጠሎ
Your browser doesn’t support HTML5
በጣይቱ ቃጠሎ አስተዳደሩና እሣት አደጋ እየተካሰሱ ነው
ላለፉት አንድ መቶ ዘጠኝ ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የኖረው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሆቴል እቴጌ ጣይቱ ሰሞኑን ባጋጠመው ቃጠሎ ከደረሰበት ጉዳት ለማደስ ጥረቶች እንደሚጀመሩ የሆቴሉ አስተዳደር አስታውቋል።
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሩም የተቃጠለውን ሆቴል ጎብኝተዋል።
በሌላ በኩል የእሳት አደጋ ሠራተኞች የሆቴሉን ጉዳት ለመቀነስ ተገቢውን ጥረትና መነሳሳት አላሳዩም ሲል የሆቴሉ አስተዳደር ወቅሷል።
ወቀሳውን ያልተቀበሉ የአዲስ አበባ የእሳት አደጋ መከላከያና መቆጣጠሪያ ባለሥልጣን “የእኛን አሠራር ካለማወቅ የተሰጠ ወቀሳ ነው” ብለዋል።
እስክንድር ፍሬው ዝርዝሩን ልኳል።