አፍጋኒስታን ውስጥ፣ አንድ አጥፍቶ ጠፊ፣ ቦምብ የያዘች መኪናውን፣ ከአንድ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶ/ ወታደራዊ ተሸርካሪ ጋር ዛሬ በማላተም፤ አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን የውጪ አገር ወታደሮችና የአፍጋኒስታን ሲቪሎች ማቁሰሉን፣ ባለሥልጣናት አስታወቁ።
ዋሺንግተን ዲሲ —

በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በሚካሄደውና ባግራም ውስጥ በሚገኘው ወታደራዊ ጦር ሰፈር ላይ የደረሰውን ጥቃት፣ ታሊባን “እኔ ነኝ” ያደረግሁት ብሏል።
የቆሰሉት ሰዎች ወዲያውኑ እዚያው ባርግራም ውስጥ ወደሚገኘው ሐኪም ቤት የተወሰዱ መሆኑንና፣ አደጋው ግን በማናቸውም ሕይወት ላይ የሚያሰጋ አለመሆኑ ታውቋል።