የዩናይትድ ስቴትስ ጦር የታሊባን ምሽግ ላይ ጥቃት አካሄደ

  • ቪኦኤ ዜና
የዩናይትድ ስቴትስ ጦር፣ ደቡባዊ አፍጋኒስታን ክፍለ ሀገር ሄልማንድ ውስጥ በሚገኝ የታሊባን ምሽግ ላይ ከባድ ጥቃት ማካሄዱ ተገለፀ።

የዩናይትድ ስቴትስ ጦር፣ ደቡባዊ አፍጋኒስታን ክፍለ ሀገር ሄልማንድ ውስጥ በሚገኝ የታሊባን ምሽግ ላይ ከባድ ጥቃት ማካሄዱ ተገለፀ።

ዛሬ ሐሙስ የወጣ ኦፊሴላዊ መግለጫ እንዳመለከተው፣ ሙሳ ቃለ ወረዳ ውስጥ የተካሄደውን ጥቃት ያደረሰው የዩናይትድ ስቴትሱ ደቡባዊ ምዕራብ ግብረ ኃይል ነው። ጥቃቱ ስላደረሰው የጉዳት መጠን መግለጫው ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጠም።

ጥቃት የደረሰበት ጠቅላይ ዕዙ፣ የታሊባን ታዋቂ መሪዎች ዋና የመሰባሰቢያቸው ማዕከል እንደሆነም ተገልጧል። በዚህ ሥፍራ የታሊባን ሠራዊት በአፍጋኒስታኒን ብሔራዊ መከላከያና ደኅንነት ኃይል ላይ ስለሚያካሂዱት ጥቃት የሚመክሩበት ሥፍራ እንደሆነም ታውቋል።