ታይዋን ምንም እንኳ በዚህ ዓመቱ የዓለም ጤና ምክር ቤት ጉባኤ በቻይና ጣልቃ ገብነት የተነሳ ባትጋበዝም፣ ከስብሰባው ጎን ለጎን ሁሉንም የዲፕሎማሲና ባህላዊ ግንኙነቶች አቅሟን በመጠቀም ተጽእኖ ለማሳደር እንደምትሞክር ዛሬ ዓርብ በሰጠችው መግለጫ አስታውቃለች፡፡
ታይዋን ከአብዛኞቹ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተገለለችው ቻይና በዲሞክራሲያዊ መንገድ የምትመራውን ደሴት እንደግዛት አድርጋ በመውሰድ በምታሰማው ተቃውሞ ነው፡፡
በታይፔ ንግግር ያደረጉት የታይዋን ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ቺዩ ታይ-ዩዋን፣ የታይዋን ልዑካን ቡድን ከወዳጅ ሀገራት ጋር ለመሰብሰብ ወደ ጄኔቭ ይሄዳል።
ታይዋን እ.ኤ.አ. ከ2009 እስከ 2016 ከቻይና ጋር ታሪካዊ የንግድ እና የቱሪዝም ስምምነቶችን ባደረጉት የወቅቱ ፕሬዝዳንት ማ ዪንግ-ጁ አስተዳደር ዘመን በዓለም ጤና ድርጅት ጉባኤ በታዛቢነት ተሳትፋለች።
ቤጂንግ የታይዋንን ተሳትፎ ማገድ የጀመረችው እኤአ በ2017፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ታይ ኢንግዌን ካሸነፉ በኋላ ነው፡፡
ፕሬዝዳንቱ ቻይና እና ታይዋን ሁለቱም "የአንድ ቻይና" አካል ናቸው በሚለው የቻይና አቋም ባለመስማማታቸው ቻይና ደስተኛ አልሆነችም፡፡