የራድዮ መጽሔት በረከት ለታደሰ ሙሉነህ፣

ድምፀ-ነጎድጓዱ አንጋፋ ጋዜጠኛ ታደሰ ሙሉነህ፣ ለዘለዓለም ሲታወስ ይኖራል

የራድዮ መጽሔት ፕሮግራምን እንደጀመርን፤ ብዙ አድማጮች ያዲሳባውን የእሁድ ጠዋት ፕሮግራም ይመስላል» ብለው የጻፉልን ትዝ ይለናል። ያን አስተያየት ዛሬ ማመን ፈለግንና፣ እንግዲያውስ የዛሬውን ዝግጅት ለምን ለዚያ፣ የእሑድ ጠዋት ፕሮግራምን ለጀመረው ለታደሰ ሙሉነህ መታሰቢያ አናደርገውም?» ብለንም ወሰንን።

የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የአማርኛው ቋንቋ አገልግሎት፣ የዛሬ ሰኔ 3 ቀን 2004 ዓም የራድዮ መጽሔት ዝግጅቱን ለታዴ ማስታወሻ አውሎታልና፣ እነሆ ቀጥሎ ቀርቧል።