ከዐስራ ሦስት ዓመታት በፊት በሀገራቸው የተቀሰቀሰውን ጦርነት ሸሽተው በተለያዩ ጊዜያት ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱ ሦሪያውያን፣ የፕረዝደንት በሽር አል አሳድ መንግሥት በመውደቁ ደስተኞች መኾናቸውን ገልጸዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከሚኖሩ ስደተኞች አንዳንዶቹ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት አስተያየት፣ “ሀገራችን ሰላም ከሆነች፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ መመለስ እንፈልጋለን” ብለዋል፡፡ ኾኖም፣ “ከአሁኑ መታየት ጀምሯል” ያሉት የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ደግሞ እንዳሳሰባቸው ይገልፃሉ።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።