ዋሺንግተን ዲሲ —
በሶሪያ የፕሬዚዳንት ባሻር አል አሳድ መንግሥት የኮሮናቫይረስን ቀውስ በመከላከል ስም አፈናውን እያጠበቀ መሆኑን ታዛቢዎች ተናግረዋል።
ሃምሣ ዘጠኝ ሰዎች ለቫይረሱ መጋለጣቸውንና ሦስት ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን የሶሪያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ቢገልጽም የምዕራባውያን የመረጃ ሰዎች ግን ይህ ቁጥር “እጅግ አንሶ የተነገረ ነው” ይላሉ።
የኮሮና ወረረሽኝ የስደተኞችን መጠለያ ጣቢያዎችና የጦርነቱ ቀውስ በተባባሰባቸው የሰሜን ምዕራብና ሰሜን ምስራቅ ሶሪያ አካባቢዎች ላይ የበለጠ ችግር እንዳይፈጥርም ተሰግቷል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5