የሶሪያን ጦርነት ለማክተም የመንግሥትና ተቃዋሚዎች አዲስ ዙር ድርድር

  • ቪኦኤ ዜና
ለስድስት ዓመታት ሲካሄድ የቆየውን የሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ለማክተም የታለመውና የሀገሪቱ መንግሥትና ተቃዋሚዎች አዲስ ዙር ድርድር ዛሬ ማክሰኞ ጂኒቫ ላይ ይከፈታል፡፡

ለስድስት ዓመታት ሲካሄድ የቆየውን የሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ለማክተም የታለመውና የሀገሪቱ መንግሥትና ተቃዋሚዎች አዲስ ዙር ድርድር ዛሬ ማክሰኞ ጂኒቫ ላይ ይከፈታል፡፡

እኤአ ከ2011 የዓረቦች ዓመፅ የሶሪያ ፕሬዚደንት ባሻር አል አሳድ ባካሄዱት ጥቃት ቁጥሩ ወደግማሽ ሚሊዮን ሰው ተገድሏል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሶሪያ ልዑክ ስታፋን ዲ ሚስቱራ ሰሞኑን የቦምብ ድብደባ መካሄዱ ስጋት ቢፈጥርም “እነሆ አሁን ወሳኙ ወቅት መጥቷል” ማለታቸው ተጠቅሷል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃል አቀባይ አሌሳንድራ ቬሉቺ ዛሬ እንደተናገሩት የሶሪያ መንግሥት መልዕክተኞች እስካሁን ጄኔቫ አልደረሱም፣ ነገ ሊገቡ አቅደዋል።

ያም ቢሆን የመንግሥታቱ ድርጅት ሸምጋይ ዲ ሚስቱራ ዛሬ ከተቃዋሚ መልዕክተኞች ጋር ስብሰባ ያካሂዳሉ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡ `

Your browser doesn’t support HTML5

የሶሪያን ጦርነት ለማክተም የመንግሥትና ተቃዋሚዎች አዲስ ዙር ድርድር