እስራኤል በሶርያ የአየር ሠፈር ላይ ባካሄደችው የአየር ድብደባ አንድ ወታደር ሲገደል ሁለት እንደቆሰሉ አንድ የመሳርያ መጋዘን ደግሞ እንደወደመ የሶርያ የመንግሥት ሚድያ ዘግቧል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በማዕከላዊ ሆምስ ክፍለ-ሀገር በሚገኘው T4 በተባለው የአየር ሰፈር ጥቃት የተፈፀመው እስራኤል በጎላን ጉብታዎች ላይ የአየር ድብደባ ከአካሄድች ሰዓታት ካለፉ በኋላ ነው።
እስራኤል በአየር ሰፈሩ ላይ ተካሄደ ስለተባለው የአየር ድብደባ የተናገረችው ነገር የለም። በጎላን ጉብታዎች ላይ ስለተፈፀመው ድብደባ ግን ባለፈው ቅድሜ ሌሊት ከሶርያ ለተተኮሰው ሮኬት ምላሽ ነወ ብላለች።
የሶርያን የሰብዓዊ መብት ጉዳይ የሚከታተለል ቡድን እንደሚለው ከሆነ እስራኤል በጎላን ጉብታዎች ላይ በአካሄደችው የአየር ድብደባ የሶርያ ወታደሮችና የውጭ ተዋጊዎች የሚገኑባቸው 10 ሰዎች ተገድለዋል።