ግብፅ ምዕራባዊ በረሃ ውስጥ የፀጥታ ኃይሎችዋ አሥራ ሁለት ፅንፈኛ ተዋጊዎችን ገድለዋል ስትል አስታወቀች።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ግብፅ ምዕራባዊ በረሃ ውስጥ የፀጥታ ኃይሎችዋ አሥራ ሁለት ፅንፈኛ ተዋጊዎችን ገድለዋል ስትል አስታወቀች።
የግብፅ መንግሥት የዜና አገልግሎት ሚና ባወጣው ዘገባ በዛሬው ዕርምጃ በፖሊሶች ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ገልጿል።
የተኩስ ልውውጡ የተካሄደው ከካይሮ በስተደቡብ ምዕራብ አንድ መቶ ሰባ አምሥት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።