አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ በሚገኙ የዲፕሎማቲክ መኖሪያ አካባቢዎች የደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታ ስምንት ሰዎች ገድሎ ሌሎች አያሌ ማቁሰሉን፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባለሥልጣናት አስታወቁ።
አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ በሚገኙ የዲፕሎማቲክ መኖሪያ አካባቢዎች የደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታ ስምንት ሰዎች ገድሎ ሌሎች አያሌ ማቁሰሉን፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባለሥልጣናት አስታወቁ።
ለጥቃቱ፣ እራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው ቡድን ኃላፊነቱን ወስዷል።
ከዚህ ቀደም አጥፍቶ ጠፊ እዚያው ዋና ከተማዋ ካቡል አቅራቢያ በሚገኝ ወታደራዊ ጦር ሰፈር ላይ ባደረሰው ጥቃት፣ 15 ካዴቶች ሞተው ሌሎች በርካታ መቁሰላቸው አይዘነጋም።
ለዚያ መኪና ላይ ተጠምዶ ለደረሰ የቦምብ ፍንዳታ፣ ታሊባን ነበር ኃላፊነት የወሰደው።
በተመሳሳይ ሳምንት ሌላ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት በአንድ የሺዓይቶች መስጂድ ላይ ደርሶ 50 ምዕመናን መሞታቸውም ይታወሳል።
እስላማዊው መንግሥት ኃላፊነቱን እንደወሰደም በወቅቱ ተገልጧል።