የሰው ህይወት ስላጠፋው የፋብሪካ ፍንዳታ የሱዳን መንግሥት ምርመራ ጀመረ

  • ቪኦኤ ዜና
የሱዳን መንግሥት ትናንት ዋና ከተማዋ ካርቱም በሚገኝ ፋብሪካ ቢያንስ ሃያ ሦስት ሰው ስለገደለው ፍንዳታ ምርመራ እንዲከፈት አዟል።

ሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ፈብሪካ ላይ በደረሰ ፍንዳታ ብዛት ያላቸው ሰዎች ተጎድተዋል። መጀመሪያ ላይ በወጡ ዘገባዎች መሰረት ጋዝ የጫነ መኪና ላይ በደረሰ ቃጠሎ ነው ፍንዳታው የደረሰው።

ሱዳን ውስጥ በበቅርብ ወራት በኢንዱስትሪዎች ላይ በተደጋጋሚ አደጋ እየደረሰ መሆኑ ተስተውሏል። መነሻው የጤና እና የደኅንነት ደምቦች ደካማነት ነው የሚለው ስጋት ጨምሯል።