በሱዳን ቢያንስ ስድስት ሰዎች ተገድለዋል

  • ሰሎሞን ክፍሌ

Sudanese demonstrators flash the victory sign as a military police vehicle drives past them during a protest demanding Sudanese President Omar Al-Bashir step down in Khartoum, Sudan, April 6, 2019.

በሱዳን ለወራት የዘለቀው ጸረ-መንግሥት ተቃውሞ ባሳለፍነው ሳምንት ማብቂያ ላይ በሺዎች የተቆጠሩ ሰዎች በወታደራዊ ጦር ሠፈሮች ደጃፍ የመቀመጥ አድማ በመምታታቸው ወደ ከፋ ደረጃ አድጓል።

ሰልፈኞች ፕሬዘዳንቱ ኦማር አል-ባሺር ሥልጣን እንዲለቁ ጥሪ እያቀረቡ ባለበት ወቅት የመንግሥቱ ጸጥታ ኃይሎች ሰልፈኞቹን ለመበትን ሲሞክሩ ወታደሮች ድንገት ሳይጠበቅ ጣልቃ ገብተው የመንግሥቱን ጸጥታ ሃይሎች ተጋፍጠዋል። በድንገቱ በትንሹ ስድስት ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፡ ሰላም ካልሰፈነ ዳግም ጣልቃ እንደሚገባ ጦር ሠራዊቱ አስጠንቅቋል።

ከካርቱም - የናባ ሞሒዲን ዘገባ ሰሎሞን ክፍሌ አጠናቅሮታል።

Your browser doesn’t support HTML5

በሱዳን ቢያንስ ስድስት ሰዎች ተገድለዋል