ዋሺንግተን ዲሲ —
Your browser doesn’t support HTML5
ዓለምአቀፉ የወንጀል ችሎት - አይሲሲ አቃቤ ሕግ ዳርፉር ውስጥ የሚያካሄዱትን ምርመራ ለጊዜውም ቢሆን እንደሚያቋርጡ ከገለፁ በኋላ የሃገሪቱ “ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር ንፁህ ሰው ስለመሆናቸው ማረገገጫ ነው” ሲሉ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አሕመድ ቢላል አስታውቀዋል፡፡
የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አልበሽርን “የሰላም ሰው” ብለዋቸዋል ዛሬ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ፡፡
ዳርፉር ላይ ሲያካሂዱ የቆዩትን ምርመራ እንደሚያቆሙ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ፋቱ ቤንሱዳ ያሳወቁት “ለጊዜውም ቢሆን” በሚል ቢሆንም የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ግን ይህ የቤንሱዳ ውሣኔ ከኦማር ሁሴን አል በሽር የሚገኝ “አንዳች ጥፋት ላለመኖሩ ማረጋገጫ ነው” ሲሉ የድል ብሥራት ከማውጣት አልቦዘኑም፡፡
አቃቤ ሕጓ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ባለፈው ሣምንት ሲናገሩ ምርመራቸውን የሚያቋርጡት አንድም ባለፉት አሥር ዓመታት ማንም ፍትሕ ፊት ቀርቦ፣ ደግሞም የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱም እርምጃ ሲወስድ ባለማየታቸውን መሆኑን አስታውቀው ነበር፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡